ከአንድነት ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት የአማርኛ ትምህርት ክፍል የተላለፈ መልዕክት

 • -

ከአንድነት ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት የአማርኛ ትምህርት ክፍል የተላለፈ መልዕክት

Category : News

እንደሚታወቀው በ፳፻፱ ዓ.ም. የትምህርት ዘመን በትምህርት ክፍሉ የተለያዩ ስራዎች ተከናውነዋል ፡፡ለአብነት ያህልም፡-

 • የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ የሚለጠፉ ጥያቄዎችን አዘጋጅቶ ተማሪዎች ለጥያቄዎቹ መልስ ጽፈው እንዲያመጡ አድርጓል፡፡
 • የስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች የሀገር ፍቅር ቲአትር ቤትን ጎብኝተዋል፡፡
 • ለተማሪዎች የሚጠቅሙ መጻህፍት ተገዝተዋል፡፡ወደፊትም ቤተ-መጻህፍቱ የተለያዩ የአማርኛ መጻህፍት እንዲሟላ ጥረት ያደርጋል፡፡
 • በየአመቱ ለአንድ ሳምንት የሚከበረው የአማርኛ ሳምንት ኢትዮጵያ ‹‹የራሷ ፊደልና ቁጥር ያላት ብቸኛዋ አፍሪካዊት አገር››Ethiopia ‹‹The only country in Africa with its own unique alphabet and numbers.›› በሚል መሪ ቃል የየክፍሉ ተማሪዎች የተለያዩ ዝግጅቶችን አቅርበዋል፡፡
CI5A8357-2

የአምስተኛ ክፍል ተማሪዎች ፉከራና ሽለላ ካቀረቡ በኋላ የተነሱት ፎቶ

CI5A8409-2

የስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች ድራማ ካቀረቡ በኋላ የተነሱት ፎቶ

ከቀረቡት ዝግጅቶች መካከል፡-

 • ግጥም
 • እንቆቅልሽ
 • እንካሰላንቲያ
 • ድራማ
 • ቀልድ
 • ፉከራና ሽለላ
 • መዝሙር የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡

   እነዚህ ዝግጅቶች ተማሪዎችን ከማስተማር ባለፈ አዝናኝና አስደሳች ነበሩ ፡፡በተማሪዎች አዕምሮም ጥሩ   ትዝታን የሚጥልና በናፍቆትም የሚጠበቅ ሳምንትም ሆኖ አልፏል፡፡

ትምህርት ክፍሉ በየጊዜው ለውጥ እያሳየ መጥቷል፡፡ለዚህም ማሳያው ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በየጊዜው አመርቂ ውጤት እያስመዘገቡ ነው፤ለትምህርቱም ፍቅር እያሳዩ ነው ፡፡ይህም የሆነው በትምህርት ክፍሉ ያሉ መምህራን ባደረጉት ከፍተኛ ትጋት እና የትምህርት ቤቱ  ርዕሰ መምህር ባደረጉት አስተዋጽኦ የተነሳ ነው፡፡

የአማርኛ ትምህርት ክፍል

 

 

 

 


Event Calendar

< 2020 >
April
MTuWThFSS
  12345
6789101112
13141516171819
20212223242526
27282930